Ifnus Construction PLC

Ifnus Construction PLC Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ifnus Construction PLC, Alibira, Adama.

Ifnus Construction:

Ifnus construction is a General construction (GC -5) company registered and licensed under the existing authorizing ministries in Ethiopia to execute the both Roads and Building/

01/11/2024

work Team work

05/09/2024

አባ ገብረ ማርያም (አባ ቦረዳ) የቦረዳ ገዳመ ዮርዳኖስ አበምኔት

አባ ገ/ማርያም በሚወዷቸው በአቡነ ተክለሃይማኖት የዕረፍት ቀን የእርሳቸውም የእረፍት ቀን ሆነ፡፡ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም. የሽኝት መርሐ ግብር በቦረዳ ገዳመ ዮርዳኖስ ተፈጸመ፡፡ ምን እንላለን በሁሉም እግዚአብሔር ትክክል ነው፡፡

ከአባ ጋር በተለይ በቅርበት ከኖርንባቸው ከ1985 ዓ ም የማውቃቸውን ለእኛ የሚጠቅሙ እና አባን ማወቅ ለሚፈልጉ ትንሽ ነገር መጻፍ ፈለኩ።

1. የብዙዎች አባቶችም ሆነ ምእመናን ችግር ከሆነው ትውልድን ከፋፋይ ከሆነ አስተሳሰብ እና አሠራር፣ ከወገንተኝነት፣ ከዘረኝነት ነጻ የሆኑ የምንኩስናን ሞራል እና ልዕልና ያስጠበቁ ለአምላካቸው ታምነው የኖሩ ድንቅ አባት ነበሩ፡፡

2. አባ ዛሬ የሽኝት መርሐ ግብር ላይ የሕይወት ታሪካቸው እስከሚነገር ድረስ ማንም የት እንደተወለዱ እና ዘራቸውን የሚያውቅ ሰው የለም፡፡ ዛሬም ቢሆን ትክክለኛ ወረዳቸውን እና እናትና አባታቸውን ሙሉ ስም የሚያውቅ የለም፡፡
(ይህ የሕይወት ታሪካቸው ከብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ጋር ያመሳስላቸዋል።)
በአንድ ወቅት አንድ ትልቅ አባት (ሊቀ ጳጳስ) እንደው አባ ገ/ማርያም የየት አካባቢ ሰው ናቸው ብለው ጠይቀውን ነበር፡፡ ነገር ግን ሊያውቅ የሚችል ሰው እንደሌለ ነግረናቸው ነበር፡፡

3. አባ እጅግ በጣም ድንቅ እና የሚያስተምር የልጅነት እና የአብነት ት/ቤት ታሪክና ትዝታ አላቸው፡፡ ነገር ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ የአካባቢውን ስም እና ቦታ ከመናገር ይጠነቀቁ ነበር፡፡

4. አባ ነገሮችን የሚያዩበት መንገድና ችግር ሲከሰት ችግሩን የሚፈቱበት መንገድ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ አባ ዘንድ ፈተና ገጥሞት፣ ጭንቀት እና አስቸጋሪ ሁኔታ ተከስቶበት ያልተፈታለት ሰው የለም፡፡ በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ ከብዙ ሰው ይሰማ የነበረው ይኸው ነው፡፡

5. አባ ደመወዝ ተቀብለው አያወቁም፡፡ አቡነ ቀውስጦስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት ለመንቀሳቀሻ እና ለአንዳንድ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ ገንዘብ ያስፈልጎታልና ደመወዝዎን ያውጡና ይጠቀሙ ቢሏቸውም ደመወዝ ተቀብለው አያውቁም፡፡

6. አባ ሁሌም አገልጋዮችን የሚመክሩትና የሚያሳስቡት እግዚአብሔር በነጻ በሰጠን ዕውቀት፣ ጉልበት እና የመሳሰሉት ጸጋዎች ውለታው በነጻ በማገልገል መመለስ አለበት የሚል ጠንካራ እምነት ነበራቸው፡፡

7. አባ መንገድ ሲወጡ ገንዘብ የማይዙበት ጊዜ ይበዛል፡፡ በጣም የሚገርመው ትራንስፖርት የሚጠቀሙት ያለምንም ስጋት ነበር፡፡ ሒሳብ ተቀባዩ እሳቸው ጋር ሲደርስ አባ የእርስዎ ተከፍሏል የሚል መልስ በተደጋጋሚ የሚገጥማቸው መልስ ነበር፡፡

8. አባ ታቦትን አቁሞ መለመን እና የቤተክርስቲያን ቅዱሳት ሥዕላትና ታቦት ማክበሪያዎችን ለልመና መጠቀም ፈጽሞ መከልከል አለበት የሚል ጽኑ እምነት አላቸው፡፡ በገዳሙ ክብረ በዓላት ላይ ታቦት ቆሞ ልመና አይካሄድም፡፡ በዣንጥላ ገንዘብ አይሰበሰብም፡፡

9. አባ ያልተናገሯቸው ለእርሳቸው ብቻ የተገለጸላቸው ብዙ ምስጢሮች ነበሩ፡፡ ነገር ግን አንዳንዶቹ በአጋጣሚና ግልጽ እንዲወጡ ከፈለጓቸው ውስጥ የቅድስት ሥላሴን ሕንፃ ቤተክርስቲያን እያሠሩ በነበረበት ወቅት ከሞጆ ለመጣው የግንባታ ባለሞያ ረዳት የሚሆኑ ባለሞያዎችን ከቦረዳ ከተማ አስመጥተን ሥራው እንደተጀመረ አንድ ቀን አባ ለግንባታው የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ለመግዛት አዲስ አበባ እንደወጡ የግንበኞቹ ቱንቢ ጠፋ፡፡ በመሆኑም በእለቱ አባ በነበሩበት ሆነው 2 መናንያን የሚሠራውን ቤተክርስቲያን ጣሪያ እየነቀሉ ያያሉ፡፡ በመጨረሻም እነዚሁ መናንያን ቱምቢውን እንደደበቁ ታውቋል፡፡፡፡

10) በቦረዳ ወረዳ እና ዙሪያው በሚገኙ ምእመናን ያላቸው ስፍራ በእውነት ታላቅ ነው። አባቴ የማይላቸው እርሳቸውም በፍቅር ዓይን የማያዩት የለም። በተለይም ወደ ገዳሙ ለሱባኤ የመጣውን የልቡን ቋጠሮ የተጨነቀውን ሁሉ ፀጉሩን እያሻሹ ዝግግ ባለ ድምፃቸው መላ ብለው ይመልሱታል።

11) ከከተማ ርቀው የሚገኙ መካነ ስብከት የተሰበሰቡ አማኞችን ጎብኝተው አስተምረው ባርከው መመለስ ቋሚ ግብራቸው ነው። ከሀገረ ስብከትም ታዝዘው የመሠረት ድንጋይ ያኖራሉ።

12) ገጠር አቢያተ ክርስቲያን በባዶ እጃቸው አይጎበኙም መብዓ ከገዳማቸው ይዘው ይወጣሉ። የገዳም አባ ይመጣሉ ከተባለ ጳጳስ እንደመጣ ይታሰባል። ልዩ ፍቅር እና ክብር።

13) አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ (Water Technology Institute በሚባልበትም ጊዜ) መምህራን እና የግቢ ተማሪዎች ከአባ ጋር ጥብቅ ግንኙነት አላቸው። ከገዳሙ ደርሶ የተሳለመ ሱባኤ የገባ ወይም አባ ወደ ዩኒቨርስቲው መጥተው ከደረታቸው የሚይዟትን መስቀል ያልተሳለመ የለም።

14) የግቢ ልጆች አባ ቦረዳ ነው የሚሏቸው። ታዲያ እርሳቸውን የቀረበ ልጅ ሁሉም ርሳቸው ያወጡለት ስም አለው። ቆይቶ ሲሄድ በዚያ ስም ይጠሩታል። ያበረታቱታል። ያጽናኑታል።

15) ሕመም ያጋጠመው እርሳቸው ጋ ፀበል ቆይቶ ሲመለስ sick leave ጽፈው ይሰጡታል። ተቀባይነት ያለው ነው። እርሳቸው በዩኒቨርስቲው ቋሚ አባት ናቸውና።

16) ዩንቨርስቲው ከሚጠሯቸው የክብር እንግዶች መካከል አባ ገብረማርያም ቋሚ ናቸው። የማይቀሩ የልጆች አባት።

17) በልጆቻቸው ቅዱስ ቁርባን ጋ ሲደርሱ ታዲያ ፈቃድ ይጠየቃሉ። ዘዉ ተብሎ አይመጥጣም። በዚያች ፈገግታቸው ምልክት ይሰጣሉ።

18) ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሥራ ማከናወን የሚችሉ አባት ናቸው። አንድ ወቅት ከገዳሙ ቅርብ መብራት ችግር አልፈታ ላላቸው የሌላ ቤተ እምነት "እኛ መብራት አግኝተን እናንተማ አይጨልምባችሁ" ብለው አባ እስከ ሀዋሳ በመሄድ አስጨርሰውላቸዋል።

19) ቀዳሽ አራሽ የሆኑ አባታችን አንድ ወቅት ጣታቸውን ተጎድተው ሳለ አባ አሁንስ ዕረፍት ይውሰዱ ሲባሉ "መናኝን ስንፍና ላስተምር?" በማለት ወደ ተግባራቸው የሚያተኩሩ አባታችን ናቸው።

20) ከአከባቢው ድልብ በሬ የገዳም አራሽ በሬ ተሽሎ ይታያል። ሁሌም የሚገርመን ነው። አቅማቸው በሕመም እስኪያዝ ድረስ ከማረስ አላረፉም።

21) መናኝን ለሱባኤ የሄደውን ሰው ይህን ሥራ ሥራ ከማለት ይልቅ ለራሴ መዳን እሠራለሁ። አንተም ለራስህ ስትል ሥራ ነበር የሚሉት።

(22)10. አባን ብዙ ጳጳሳት ለጵጵስና ፈቃደኛ እንዲሆኑ ጠይቀዋቸው ነበር፡፡ አባ ግን መልሳቸው እምቢታ ነበር፡፡ አንድ አባት በተደጋጋሚ የሕይወት ታሪክዎን በአስቸኳይ ጽፈው ይስጡኝ ሲሏቸው አባ እሺ በማለት ጊዜ መግፋት ነበር የተያያዙት በኋላ እኚሁ አባት ቢቸግራቸው እኔ ራሴ ገዳም መጥቼ እቀበልዎታለሁ ብለው ነበር፤ አባ ግን እኔ ስጽፍ አይደል የሚቀበሉት ብለውን ነበር፡፡

በሌላ ጊዜ ስማቸውን መጥቀስ የማያስፈለግ አባት አንድ ቄስ እንደ ሽማግሌ ልከውባቸው እምቢ በማለታቸው ቄሱም እስቲ እናንተ አናግሯቸው ብለውን ነበር፤ አባ ለምን እምቢ አሉ ስንላቸው እስቲ ተመልከቱ እኔ በዚህ በምንኩስና በገዳም መሥራት የነበረብኝን አገልግሎት በአግባቡ ሳላከናውን ጳጳስ ሆኜ ምንስ ልሠራ ነው? የያዝኩትን ያልሠራሁ ጵጵስና የማይገባኝ ነኝ የሚሉ አባት ነበሩ፡፡

(23)11. አባ በዚህ እድሜ በሬ ጠምደው እርሻ የሚያርሱ ሲሆን ድንቅ በሚባል ሁኔታ እህል አፈራርቆ መዝራትን በአግባቡ የተረዱ እና የትኛው እህል ከየትኛው በኋላ መዘራት እንዳለበት ጠንቅቀው የሚያውቁ ምርጥ የግብርና ባለሞያ ናቸው፡፡

24) የአባ ልዩ ጸጋ ሌሊት ሰዓታት አድረው ከኪዳን መልስ ወደ ዕረፍት ሳይሆን ወደ እርሻ ነው፤ በእርሻ ቦታ አባ ሥራቸው ማረስ ወይም አረም ማረም ብቻ ሳይሆን ተማሪዎቻቸውን ማስተማርም ጭምር ነው፡፡ በእርሻ ቦታ ሌላው እያረሰ እርሳቸው ቁጭ ብለው የሚያስተምሩ እንዳይመስላችሁ ተማሪዎቻቸው ከእርሳቸው ሥር ሥር እየተከተሉ ንባቡን፣ ቅዳሴውን፣ ሰዓታቱን ያስቀጥሏቸው ነበር፡፡ ከእርሻ መልስ ሰባት ሰዓት ሲደርስ ያለምንም እረፍት ወደ ቅዳሴ ይገባሉ፡፡ ከቅዳሴ መልስ ቀን የተሠራውን ከገመገሙ በኋላ 12 ሰዓት ሲሆን መደበኛ ትምህርት ወንበር ዘርግተው ማስተማር ይጀምራሉ፣ ይህ ደግሞ እስከ ምሽቱ 4 እና 5 ይቀጥላል፡፡ ይህ አገልግሎት ሁሌም የሚከናወን መደበኛ አገልግሎታቸው ነው፡፡

በተጨማሪም አባ ምርጥ የግብርና ባለሞያ የሚያሰኛቸው ዘመናዊ የእህል ጎተራ ሠርተው ተግባራዊ ያደረጉና የወረዳውና የዞን የግብርና ባለሞያዎች እንደ ተሞክሮ ልምድ የሚወስዱበትና ለሥልጠና መስጫነት የሚጠቀሙበት መሆኑ ነው፡፡

25) አባ የግብርና ብቻ ሳይሆኑ የሕንጻ ምህንድስና ጥበብም የታደሉ ናቸው፡፡ በቤተክርስቲያን ሕንጻ ሥራ እና የተለያዩ ግንባታዎችን በሚያካሂዱበት ወቅት የሚሰጡት አስተያየትና ምክር ባለሞያዎችን በጣም የሚያስገርምና የሚያስደንቃቸው ነው፡፡

መሐንዲሶቹም አባን ሁሌም የሚጠይቋቸው አባ ከዚህ ቀደም የምህንድስና ትምህርት ተምረዋል? የሚል ነው ምክንቱም የሚሰጧቸው አስተያየቶች ከአንድ ምህንድስና ከተማረ መሐንዲስ ነው የሚል ነው፡፡

26) አባ የሁሉ አባት ናቸው፡፡ ኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንት እና ሙስሊም በማለት ሰውን አይለዩም ለሁሉም ጥልቅ ፍቅር አላቸው፡፡ ለሁሉም አቅፈው በመሳም ፍጹም ፍቅርን ያለአድሎ የሚፈጽሙ አባት ነበሩ፡፡ ከብዙ ታሪኮቻቸው ለማንሳት 3 ጓደኛሞች ነበሩ፣ ሁለቱ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ሲሆኑ አንዱ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነበር፤ ነገር ግን አንድ ቀን 2ቱ ቀርበው ሲሳለሙ አንደኛው ሸሽቶ ዳር ሲቆም ና ብለው ስመው አቅፈው በመምከር ፍቅራቸውን ይገልጹለታል፡፡

በተደጋጋሚ አባን ሲያገኛቸው የሚያሳዩት አቅፈው መሳም እና ትከሻውን እቅፍ አድርገው በሚገልጹት ሁኔታ ልቡ እጅግ በመነካቱ አባን አንድ ቀን ቀርቦ አባ እኔ ኦርቶዶክስ መሆን እፈልጋለሁ አሁን ያጥምቁኝ ሲላቸው ቆይ ተምረህ ትጠመቃለህ ቢሉት አባ እኔ ከእርስዎ እምነትን ፍቅርን ሁሉንም የኦርቶዶክስ ትምህርተ ወንጌልን በተግባር አገኘሁ በሚል መልሶላቸዋል፡፡ አባም መምህር መድበው ከተማረ በኋላ ሊጠመቅ ችሏል፡፡

(27) 14. አባ ለሀገራችን ብሎም ለቤተክርስቲያናችን ዐይን የሆኑ ብዙ ሊቃውንትን ያፈሩ ሊቅ ናቸው፡፡ ያፈሯቸው ሊቃውንት ሁሉ የተመሰከረላቸው ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪና ፈጥኖ ደራሾች ናቸው፡፡ አባ ለቁጥር የሚታክቱና ይህንን ያክላሉ የማይባሉ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ አበው መነኮሳት እና ጳጳሳትን፣ የገዳማትና ደብራት አስተዳዳሪዎች ያፈሩ የሊቃውንቱ ሊቅ ነበሩ፡፡

ለምሳሌ ያህል በዚህ ዘመን በቤተክርስቲያናችን ላይ እየመጣ ያለውን ፈተና ከሌሎች አባቶች ጋር በመሆን እየተጋደሉ ከሚገኙት አባቶች አንዱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የአባ ደቀ መዝሙራቸው ነበሩ፡፡

28) አባ ለቤተ ክርስቲያን እጅግ ቀናዒ መሆናቸው ኖላዊነታቸውም ግሩም የሆነ ነው። አባትነታቸውም ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን አንጻር በደንብ የተገለጸ እና የታየ ነው፡፡

በተለይም አባ ታቦት የሚያከብሩ ዕለት ከ2 ቀናት በላይ በመጾም ነው ታቦት የሚያከብሩት፡፡

በተጨማሪም ሐምሌ 25/1985 ዓ.ም. የቅ/ሚካኤል ታቦት ከዋሻ ከመውጣቱ በፊት ለ 7 ቀናት ያህል አባ በዋሻው ውስጥ ተሰውረው ነበር፡፡ ታዲያ እንዲህ አይነት አባት ከየት ይገኝ ይሆን? በነገራችን ላይ ስለገዳሙ የመጀመሪያዎቹን ሐመር መጽሔት ማንበብ ነው።

29) አባ ፍልሰታን ሁሌም በቆሎና በውኃ ነው የሚያሳልፉት፡፡ አባ በፍልሰታ ሲያሳልፉ ትልቅ ፍቅር የሚያስይዘውና ፍልሰታን ከአባ ጋር በቦረዳ የሚያሰኘው ሰዓታቱ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ንዒን አባ ያዚሟትማ!! መቼም የዜማ መምህርም አይደሉ?! ፍልሰታን አባ ጋር ያሳለፋችሁ ይህንን ስታነቡ በዕንባ እንደምታነቡት እርግጠኛ ነኝ፡፡

ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ኀዳፌ ነፍስን "
❖አዎን አቤቱ የሁሉ አምላክ ነህ፣
❖አዎን አቤቱ የሁሉ ንጉሥ ነህ፣
❖አዎን አቤቱ ሁሉን የያዝህ ነህ፣
❖አዎን አቤቱ ሁሉን የምትገዛ ነህ፣
❖አዎን አቤቱ ሁሉን የምታድን ነህ፣
❖አዎን አቤቱ በእውነት የሁሉ ገዥ ነህ፣
❖አዎን አቤቱ የሁሉ መድኃኒት ነህ፣
❖አዎን አቤቱ ሁሉን የምትጠብቅ ነህ፣
❖አዎን አቤቱ ሁሉን የምትመግብ ነህ።" እያሉ ሲያነብቡ አቤት ጭልጥጥ እኮ የሚያደርጉን። ምን ዓይነት ጸጋ ነው?! ዓለም ኮ ነው የሚያሳዩህ።
እኚህን አባት ምን እንበላቸው?

30) በአባ ፍጹም መንፈሳዊ ሕይወት እና ትጋት ከቤተክርስቲያን በርቀት የነበሩ ክርስቲያኖች ወደ ቤተክርስቲያን እንዲቀርቡ ሆኗል፡፡ ከብዙ ሰዎች ምስክርነት የአንዱን እንኳ ብናነሣ ከቆርጋ ቦረዳ የመንገድ ሥራ የከባድ መኪና ሾፌር የነበረ አቶ ደረሰ የሚባል ሰው " አባን ሳገኛቸው እና እቅፍ አድርገው ሲስሙኝ ከውስጤ አንዳች መንፈስ ሲወጣ እና ደስታ እና እርካታ ይሰማኛል።" ይል ነበር፡፡ በዚህ የተነሳም ውስጡ ሲረበሽና ጭንቀት ሲሰማው አባ ጋር ልሂድና ሰላሜን አግኝቼ ልምጣ ይል ነበር፡፡ ይህንንም በተደጋጋሚ ይፈጽም ነበር፡፡

31) ዘራፊ ሽፍታ በጫካ ሲያገኛቸው ስንት ሰው ሲዘርፉና ሲያሰቃዩ አባን ግን አክብረው ነው የሚሸኙአቸው፡፡ በአባ ምክንያትም ከዘራፊ የተረፉና በአባ መኖር ከሞት የተረፉ ብዙ ሰዎች ናቸው፡፡

ለምሳሌ የቦረዳውን ብናነሣ 1990 መጀመሪያዎቹ አካባቢ ከወላይታ ሶዶ ወደ ቦረዳ በአይሱዚ አባ ጋቢና ተቀምጠው እየተጓዙ እያለ ዘራፊዎች ወጥተው ድንገት በክላሽ ሾፌሩ ጭንቅላቱ ላይ አነጣጥረው ይቶክሳሉ ነገር ግን ሾፌሩ አባ እግር ላይ ተኝቶ ተርፏል፡፡ የተተኮሰው ጥይት ግን የመቀመጫውን ማለትም የሾፌሩ ጭንቅላት ማረፊያውን በስቶ ነው የወጣው፡፡ የሾፌሩ ምስክርነት በአባ መኖር ከሞት ተረፍኩ ነበር፡፡

#ስለኑዛዜያቸው
የአባ ገ/ማርያም ኑዛዜ
ነሐሴ 27/2016 ዓ/ም
የገዳሙ መነኮሳትና መናኒያ ስለ ገዳሙ የወደፊት ጉዳይ እሁድ ማታ ሲወያዩ አድረው ጠዋት በገዳሙ ዙሪያ ከሚኖሩ ሽማግሌዎች እና ከገዳሙ የልማት ኮሚቴዎች ጋር ባደረጉት ምክክር መሀል የአባታችን ኑዛዜ ተሰማ
(አባ ቦረዳ) አርሶአደሩን የአከባቢውን ማኅበረሰብ የሚያስተባብሩ የልማት ኮሚቴዎችንና ሽማግለዎችን ጠርተው ወደ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ወሰዷቸው።
"ልጆቼ የአካባቢው ሰው እኔ በሌለሁበት ቢሞት ምን ታረጋላችሁ?" የቦታ ጥበት ስላለ መደዳውን በዝህ መስመር ሊቀበር ይገባል። ማንም ሰው ቦታ መርጦ ይህንን ቦታ ስጡኝ ሊል አይገባም። "እኔም ብሞት" ብለው አሁን ያረፉበትን ቦታ ነገሯቸው።
ከእኔ ቦኃላ አባ ኃይለ ሚካኤል አባት ይሁኗችሁ ገዳሙንም እንእኔ ይምሩ። ታድያ አደራችሁን ይህችን ነገር ጊዜው እስከሚደርስ ለማንም እንዳትናገሩ። ብለውናል በማለት የልማት ኮሚቴዎቻቸውና ሽማግሌዎች ለገዳሙ አባላት ነገሯቸው።
ሁሉም የገዳሙ አባላት እና ከደብረ ሊባኖስና ከሌሎች ገዳማት በመጡ የቀድሞ የገዳሙ አባላት ባሉበት ጉዳዩን መርምረው በኑዛዜው ቃል በአንድ ልብ ተደስተዋል።
ይህንንም የኑዛዜ ቃል በጽሁፍ አስፍረው ለሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሚገልጹ ሽማግሌዎችንና መነኮሳትን መርጠዋል።
በአባቶች እግር የሚተኩ ልጆችን አያሳጣን።

ልዩ አባት!!!
በረከታቸው ይደርብን!!!!

በመምህር ጌትነት አስራቱ ፅሁፍ ትንሽ ተሻሽሎ የቀረበ!!!

31/08/2024



የገዳመ ዮርዳኖስ ቅድስት ሥላሴና ቅዱስ ሚካኤል አበ ምኔት (አስተዳዳሪ) የነበሩት የጸሎት አባት አጽናኛችን አባ ገብረ ማርያም (አባ ቦረዳ) ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡

ጸሎታቸው ማኅበራችንን ይጠብቅልን፤ በረከታቸው ይደርብን፡፡

ወልደ ተክለሃይማኖት አባ ገብረ ማርያም ዘቦረዳ
ወ - ይ እንባ ወይ እንባ ፤ ከአይኔ ይፍሰስ፣
ል - ቤ ይቁሰል ይድማ ፤ ሰማዩን ይክሰስ፣
ደ - ረቴንም ልድቃው ፤ ለአባቴ ላልቅስ፡፡

ተ - ክልዬ ሲያደላ ፤ እራሱን ሲውድድ፣
ክ - ቡር ሞቱ ለጻድቅ ፤ ከራሱ ሊያዋድድ፤
ለ - ኖረ እርሱን መስሎ ፤ በተገፋ ምድር፣
ሃ - ያ አራት ነሐሴ ጠራው ፤ አረፈ በክብር፡፡
ይ - ደንቃል ዕጹብ ነው ፤ እስከሞት አንድነት፣
ማ - ንባቱ ይብቃና ፤ በአርምሞ ሆነን እንደነቅ በእውነት፡፡
ኖ - መ ኖመ ኢየሩሳሌም በፍስሐ ወበሰላም ፣
ት - ንብልናሁ ወአስተብቊዖቱ ይዕቀበነ ለዓለም፡፡

አ - ባ ገብረ ማርያም ፤ ታዛ ነው ዋርካ ነው ፤
ባ - ርክኒ አንተ ፤ አትርሳን እንበለው፣
ገ - ዳምህ መጥተናል ፤ እጅህን ልንስመው፡፡
ብ - ርዱ የዝቋላ ፤ አይቻል ተለብሶ፣
ረ - ሳሁት አሁን ፤ የቦረዳ ብሶ፡፡
ማ - ር ጣፋጭ በምድር፤ ያም የሰማይ ድርሻ፣
ር - ስቱን ማን ያስፋው፤ ማን ይግባ ከእርሻ፣
ያ - ደጉ ገበሬ ፤ ወንጌል የሚዘራ እህል የሚዘራ፣
ም - ን ጋግሮልን ሄደ፤ ነገን እንዳይርበን የሚበላ እንጀራ፡፡

ዘ - ላለም ተጽፎ ፤ ከገዳሙ አፈር፣
ቦ - ረዳ ሚካኤል ፣ ቦረዳ ሥላሴ ፤ ስምህ ነው ሚዘከር፡፡
ረ - ዳት የሚሆን ፤ ኃዘን የሚያስረሳ፣
ዳ - ግማዊ ቦረዳ ፤ ሚካኤል ያስነሳ፡፡

ነሐሴ 24 – 2016 ዓ.ም
(ከፌስቡክ ገፅ የተወሰደ)

ዛሬ ገና ባዶነት ተሰማኝ። አባቴ በረከቶ ትደርብኝ። .. (ደካማው ልጆ!)እንባስ ለኔዉዋይታም ለኔማዘንም ለኔዉለደካማዉ።..........
31/08/2024

ዛሬ ገና ባዶነት ተሰማኝ።
አባቴ በረከቶ ትደርብኝ።
.. (ደካማው ልጆ!)
እንባስ ለኔዉ
ዋይታም ለኔ
ማዘንም ለኔዉ
ለደካማዉ።..........

THE LIGHTER
29/01/2023

THE LIGHTER

Ethiopian Great Jobs African Diplomatic Capital Addis Ababa Ethiopia 🇪🇹😍Mesob _Tower Addis Ababa, EthiopiaConstruction o...
14/09/2022

Ethiopian Great Jobs

African Diplomatic Capital Addis Ababa Ethiopia 🇪🇹😍
Mesob _Tower Addis Ababa, Ethiopia

Construction of the Mesob Tower in Ethiopia is set to begin. Ethiopian Minister of Culture and Tourism revealed the report and said that the architects who designed the tower, to commence construction works.
The 70-storey development will be located in the country’s capital city, in Addis Ababa. It will be 250 metres high and will sit on a 20,000 square meters of land. The US $681m project will feature hotels, shopping malls, a cultural center representative of all regions of Ethiopia, a gym and a golf club, among other things. The development is projected to be completed in five years’ time...

https://t.me/ThePoliticalInsiders

02/08/2022
04/12/2021
Our work experience we made easy your dreams and Life!
16/12/2018

Our work experience we made easy your dreams and Life!

Address

Alibira
Adama

Opening Hours

Monday 06:00 - 17:00
Tuesday 06:00 - 17:00
Wednesday 06:00 - 17:00
Thursday 06:00 - 17:00
Friday 06:00 - 17:00
Saturday 06:00 - 17:00
Sunday 10:00 - 16:00

Telephone

+251943327002

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ifnus Construction PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ifnus Construction PLC:

Share