30/01/2026
"የአረንጓዴ አሻራ እንክብካቤ ማድረግ የተተከሉት ችግኞች ለመጪው ትውልድ የአየር ንብረት ለውጥ ሁነኛ ሚና ይጫወታል"
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለመጪው ትውልድ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥርና ተስፋን የሚሰጥ መሆኑን እና እንክብካቤ መደረግ እንዳለበት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት አስታወቀ።
በዛሬው ዕለት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት አመራርና ሰራተኞች በክረምት አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኝችን ተንከባክበዋል።
የክፍለ ከተማው ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ አበበ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የደን ሽፋን እንዲያድግ፣ የአየር ንብረት ለውጥና የመሬት መንሸራተት አደጋ እንዳይከሰት እያገደረገ ካለው አስተዋፅኦ ባሻገር ውብና ፅዱ እንዲሁም ለዜጎች ምቹ አከባቢን በመፍጠር ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።
በመሆኑም ሁሉም አካል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት ገልፀዋል።