Defense Construction Enterprise

Defense Construction Enterprise Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Defense Construction Enterprise, Construction Company, Addis Ababa.

Defense Construction Enterprise was established in 2010 by Ethiopian ministry of council regulation NO 185/2010 as public enterprise and national defense as supervising authority of the enterprise.

ኢንተርፕራይዙ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አዳዲስ ገልባጭ መኪኖችን አስገባ።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2018 ዓ.ምበኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ቅልጥፍናና ዕድገ...
14/08/2026

ኢንተርፕራይዙ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አዳዲስ ገልባጭ መኪኖችን አስገባ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ቅልጥፍናና ዕድገት ማሽነሪዎች ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው። ይህንን ብሔራዊ ዓላማ በመከተል መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ የ2024/ 2025 አዲስ ሞዴል 20 ዘመናዊ ገልባጭ መኪኖችን ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ገዝቶ ወደ ሥራ አስገብቷል።

የኢንተርፕራይዙ የግንባታ መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎች አስተዳደር እና ጥገና መምሪያ ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ሀብታሙ ደሬሳ እንደገለጹት፦

በአሁኑ ወቅት የአንድ ገልባጭ መኪና ወርሃዊ ኪራይ እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ መሆኑን ጠቁመው አዲሶቹ መኪኖች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገቡ በዓመት ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን ያስችላሉ።

ተሽከርካሪዎቹ በጂፒኤስ (GPS) የታገዘ የደህንነት ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግላቸው በመሆኑ የብልሽት ቅነሳ እንዲኖር ያስችላሉ።

ግዥው የኢንተርፕራይዙን የመፈጸም አቅም ከማሳደጉም በላይ፣ ለሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ጊዜንና ገንዘብን በመቆጠብ የደንበኞችን እርካታ እንደሚያረጋግጥ ተገልጿል።

በመጨረሻም ተሽከርካሪዎቹ የሀገር ሀብት ጭምር በመሆናቸው፣ ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታቸውን ሳይጨርሱ ለብልሽት እንዳይዳረጉ ሠራተኞችና የሥራ አመራሮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ዜና እረፍት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የአምቦ ወሊሶ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ተሾመ ደምሴ ዳዲ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም...
08/08/2026

ዜና እረፍት

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የአምቦ ወሊሶ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ተሾመ ደምሴ ዳዲ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች በአቶ ተሾመ ደምሴ ዳዲ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን፡፡

ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን!

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአዋሽ ሰባት መሠረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት የመስክ ምልከታ ተካሄደ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም.በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተር...
03/08/2026

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአዋሽ ሰባት መሠረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት የመስክ ምልከታ ተካሄደ

ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም.

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአዋሽ ሰባት መሠረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

በምልከታው ላይ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዴር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ እና የኢንተርፕራይዙ የሕንጻ ግንባታ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸናፊ ሐሰን ተገኝተው የፕሮጀክቱ ሥራ አፈጻጸም በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳና በጥራት እየቀጠለ መሆኑን ተመልክተዋል።

የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቀሪዎቹን ሥራዎች በተያዘለት ጊዜ አጠናቀን ለባለቤቱ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በፍጥነት ጨርሶ ለማስረከብ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአዋሽ ሰባት ማሰልጠኛ ማዕከል ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ኢንጂነር እሸቱ ታደሰ በግንባታው ሂደት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሥራ አስኪያጁ እንዳሉት፤ በአሁኑ ወቅት የጣሪያ፣ የበርና መስኮት ገጠማ፣ የኤሌክትሪክ፣ የሳኒተሪ እና የመንገድ ሥራዎችን ጨምሮ ቀሪ ሥራዎች በፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ። የግንባታ ፕሮጀክቱ የሚገኝበት አካባቢ ከፍተኛ ሙቀትና የዲዛይን ማስተካከያዎች ቢኖሩበትም፤ የሥራ ሰዓትን እንደየአየር ሁኔታው በማስተካከል፣ እንዲሁም የሰው ኃይልና ቁሳቁሶችን በማሟላት ሥራው ያለምንም ማቋረጥ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

የማሰልጠኛ ማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ፤ ለ4,200 ሰልጣኞች የሚሆን መኖሪያ፣ ለ900 ሰልጣኞች የሚሆን መመገቢያና ዘመናዊ የምግብ ማዘጋጃ፣ 100 የአሰልጣኞች እና 10 የመኮንኖች መኖሪያዎች፣ 8 የቢሮ ሕንጻዎች፣ ሁለገብ መጋዘን፣ መጸዳጃ ቤቶች፣ የጥበቃ ቢሮ፣ የግቢ አጥርና በር፣ ለሰልጣኞች የምረቃ አገልግሎት የሚሰጥ መድረክ እንዲሁም ከመሠረተ ልማት ጋር የተያያዙ መንገዶችን ያካትታል።

የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር  የችግኝ ተከላ  አካሂደዋል።የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ምየመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕና የመከላ...
03/08/2026

የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕና የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አመራሮችና ሠራተኞች በ8ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመሳተፍ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።

ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የዘንድሮው የክረምት አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤትና የቢሾፍቱ ሞተር ቪሂክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ አመራሮችና ሠራተኞች በቢሾፍቱ በተዘጋጀው የችግኝ መትከያ ስፍራ በጋራ በመገኘት አከናውነዋል።

በመርሃ ግብሩ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጌታቸው ኃይለማሪያም፣ የቢሾፍቱ ሞተር ቪሂክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኮሎኔል ተክሉ ፀጋዬና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።

በተመሳሳይ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አመራርና ሠራተኞች በዋና መሥሪያ ቤቱ እንዲሁም በተቋሙ በሚያከናውናቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ ለአካባቢው የአየር ፀባይ ተስማሚ የሆኑና በረሃማነትን ለመከላከል የሚያግዙ የአትክልትና የፍራፍሬ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች ተክለዋል።

የተቋማቱ አመራርና ሰራተኞች እንደገለጹት፣ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የአካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር፣ የደን ሽፋንን ለመጨመር፣ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል። ዘገባው የክፍሎቹ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሐረሪ ሪጅን ዋና ጽህፈት ቤት ህንፃ ግንባታ ተጀመረ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ምሀገራዊ የልማት አጋርነቱን በተለያዩ ጊዜያት በማ...
01/08/2026

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሐረሪ ሪጅን ዋና ጽህፈት ቤት ህንፃ ግንባታ ተጀመረ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም

ሀገራዊ የልማት አጋርነቱን በተለያዩ ጊዜያት በማስመስከር የሚታወቀው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሐረሪ ሪጅን ዋና ጽህፈት ቤት ሕንፃ ግንባታ በይፋ ጀምሯል።

በግንባታ ማስጀመሪያው መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፤ ኢንተርፕራይዙ በርካታ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በሰዓቱ የማጠናቀቅ የቆየ ልምድ ያለው ተቋም መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ላይ በይፋ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሕንፃ ግንባታም በተያዘለት የጊዜ ገደብና የጥራት ደረጃ ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን የሰው ኃይልና ማሽነሪ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን አረጋግጠው፣ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ በጥራት ተጠናቆ እንደሚረከብ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ ወይዘሮ ለምለም ምስጋናው በበኩላቸው፣ ግንባታው በመከላከያ ኮንስትራክሽን እንዲከናወን መደረጉን ጠቅሰር አዲሱ የሪጅኑ ዋና ጽህፈት ቤት ህንፃ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንደሚጠናቀቅ ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የሕንፃ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን የኃይል አቅርቦትና የመሰረተ ልማት አገልግሎት ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አክለዋል።

የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ኻሊድ ጣሀ በበኩላቸው፣ የግንባታው ሥራ በተያዘለት ጊዜና የጥራት ደረጃ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በክልሉ የሚገነባው ይህ የተቋሙ ባለ አስር ወለል ህንፃ ለግንባታው ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የተመደበለት ሲሆን፣ በቀጣዮቹ 900 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

28/07/2026
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሕንፃ ግንባታ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቅ እንዳለበት ተገለጸሐምሌ 11 ቀን 2018ዓ.ምመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በሐረር ከተማ ለኢት...
18/07/2026

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሕንፃ ግንባታ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቅ እንዳለበት ተገለጸ

ሐምሌ 11 ቀን 2018ዓ.ም

መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በሐረር ከተማ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚገነባውን የG+10 ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ለማስጀመር የሚያስችል የመስክ ምልከታ አድርጓል። በ2.1 ቢሊዮን ብር በጀት የሚገነባውን ይህን ፕሮጀክት፣ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዴር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፣ የሕንጻ ግንባታ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸናፊ ሐሰን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሐረር ቅርንጫፍ ተወካዮች እና አማካሪው ድርጅት የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በተገኙበት ግንባታ የሚከናወንበትን ቦታ ተመልክተዋል።

የግንባታ ሥራውን ለመጀመር፣ በቦታው ላይ የሚገኙ ከፍተኛ ቮልቴጅ ያላቸው የኤሌክትሪክ መስመሮችና ማከፋፈያዎች፣ የመብራት ምሰሶዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ ቁሳቁሶች፣ አሮጌው የቢሮ ሕንፃ እና ዕድሜ ጠገብ ዛፎች በአፋጣኝ እንዲነሱና የወሰን ማስከበር ሥራው እንዲጠናቀቅ፣ ከግንባታው ባለቤትና ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር በጋራ ተወያይተው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ሕንፃ ግንባታው በውስጡ የተለያዩ ቢሮዎችን፣ ዘመናዊ አዳራሾችን፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ካፌቴሪያዎችን፣ ሰፊ የመኪና ማቆሚያ እና የተለያዩ መጋዘኖችን አሟልቶ በመያዝ የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ የተሳለጠ እንደሚያደርገው ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታልና የሐኪሞች መኖሪያ አፖርትመንት ማስፋፊያ ግንባታ የመስክ ምልከታ ተካሄደሐምሌ 10 ቀን 2018ዓ.ምየመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በሐረር ከ...
17/07/2026

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታልና የሐኪሞች መኖሪያ አፖርትመንት ማስፋፊያ ግንባታ የመስክ ምልከታ ተካሄደ

ሐምሌ 10 ቀን 2018ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በሐረር ከተማ እየገነባ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታልና የሐኪሞች መኖሪያ አፓርትመንት ማስፋፊያ ግንባታ ሂደት ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

በምልከታው ላይ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዴር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ እና የኢንተርፕራይዙ የሕንጻ ግንባታ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸናፊ ሐሰን ተገኝተዋል። የፕሮጀክቱ ባለቤት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሲሆን፣ የዲዛይን፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራው በጋትሜትስ ኢንተርናሽናል እየተከናወነ ይገኛል።

በመስክ ምልከታው የሆስፒታሉ አብዛኛው ግንባታ ተጠናቆ፣ የግቢው የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ እና የዙሪያ አጥር ሥራዎች ተከናውነዋል። በአሁኑ ወቅት የሁለቱም ሕንጻዎች የመጨረሻ የፊኒሽንግ የማጠናቀቂያ ሥራ እና የግቢ ማስዋብ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ፕሮጀክቱ ያለበትን የአፈጻጸም ደረጃ በጥልቀት ገምግመዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሰጡት አቅጣጫ መሰረት፣ ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ሕንጻዎቹ ለታለመላቸው ዓላማ መዋል እንዲችሉ አስፈላጊው ጥረት እንዲደረግ የሥራ መመሪያ ተሰጥቷል። ግንባታው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ባለቤት ለሆነው ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በአጭር ጊዜ ማስረከብ እንዲቻል፣ ጥብቅ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

በሐረር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ማስፋፊያ፣ ለምሥራቅ ኢትዮጵያና ለአጎራባች አገሮች የጤና አገልግሎት ዘርፍ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ይጠበቃል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዱን ይፋ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 03 ቀን 2018 ዓ.ም የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከ2019 ...
10/07/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዱን ይፋ አደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 03 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከ2019 እስከ 2023 በጀት ዓመት የሚተገበር አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ ይፋ አድርጓል። ተቋሙ በስትራቴጂክ ዕቅዱ 61.6 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘትና የፕሮጀክቶችን የጊዜ መዘግየት ምጣኔ ወደ ዜሮ የማውረድ ግብ ሰንቋል።
ይህ ዕቅድ ተቋሙን ከዘመኑ የቴክኖሎጂ አቅጣጫ ጋር በማስተሳሰር ተወዳዳሪነቱን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

ዕቅዱ በአራት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ የተመሰተ ሲሆን የፕሮጀክት ክንውን ብቃትን ማሳደግ፣ የፋይናንስ ዘላቂነትን ማረጋገጥ፣ የዲጂታል ሽግግርና የሰው ኃይል ልማትን ማፋጠን፣ እንዲሁም የአመራር አስተዳደር ሥርዓትን ማጠናከር ናቸው።

የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ እንደገለጹት፤ ተቋሙ ኢአርፒ (ERP) እና ቢም (BIM) ቴክኖሎጂዎችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደርጋል። በተጨማሪም የማሽነሪዎችን አጠቃቀም በጂፒኤስ (GPS) በመቆጣጠር እና የሠራተኞች ፍልሰትን ከ5 ከመቶ በታች በማውረድ ውጤታማነቱን ለማሳደግ ታቅዷል።

ለስኬታማነቱም በውጤት ላይ የተመሰረተ የአስተዳደር ሥርዓት (OKR) ለመተግበር ታቅዷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዲጂታል ክትትል የታገዘ የተጠያቂነት አሠራር ተግባራዊ ይሆናል።

ለስትራቴጂክ ዕቅዱ ስኬታማነት እያንዳንዱ ፕሮጀክት እና የሥራ ክፍል ዕቅዱን ለሠራተኞች ማዳረስ፣ የሥራ አፈጻጸምን ከሠራተኛ ጋር ማገናኘት፣ እንዲሁም የድጋፍና ቁጥጥር ሥርዓትን (ቼክ ሊስት) መተግበር እንደሚገባ ተመላክቷል።

ኢንተርፕራይዙ የሚያጋጥሙትን የፕሮጀክት መዘግየት፣ የወጪ መናር እና የገንዘብ ፍሰት እጥረት የመሳሰሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታትም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል፡፡

የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዱ በኢንተርፕራይዙ የዕቅድ ዝግጅት መምሪያ ተወካይ በኮሎኔል ምንውየለት አሰፋ የቀረበ ሲሆን፣ ከስትራቴጂክ ዕቅዱ መነሻ የተዘጋጀው የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ደግሞ በአቶ ግዛው ክፍሌ ቀርቦ በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል።

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ2018 በጀት ዓመት ውጤታማ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለጸ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 01 ቀን 2018 ዓ.ም የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕ...
08/07/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ2018 በጀት ዓመት ውጤታማ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለጸ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 01 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከመሥሪያ ቤት አመራሮች፣ ከፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች እና ከቡድን መሪዎች ጋር ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ውይይት አካሂዷል።

በ2018 በጀት ዓመት ፕሮጀክቶችን በመምራት፣ በማስተዳደር እንዲሁም አጠናቆ ለምረቃ በማብቃት ረገድ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል። በበጀት ዓመቱ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመረከብ፣ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን በማጠናከር ፋይናንሳዊ ጤናማነትን ለማረጋገጥ፣ የሀብት አጠቃቀምንና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እንዲሁም የሥራ አካባቢን ምቹ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸው ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ የሰው ኃይል ልማትንና አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ፣ የማሽነሪና ተሽከርካሪ ጥገና አቅምን ለማሳደግ፣ ሥራዎችን አቀናጅቶ ለመሥራት እንዲሁም ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከል በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል።

ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ ማብራሪያ የሰጡት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ፤ በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ ሥራዎች ውጤታማ ከመሆናቸውም ባሻገር፣ ለቀጣይ ሥራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ዘርፎች የተለዩበት ወቅት እንደነበር ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በቀጣይ መስተካከል ያለባቸውን ጉድለቶች በማረም ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንደሚገባና በሁሉም የሥራ ዘርፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Defense Construction Enterprise posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share