Yirgalem Construction

Yirgalem Construction Yirgalem Construction is a Grade–1 General Construction Company which
is established as a sole proprietor in 1989 E.C. Operating for over 30 years.

engaged in Buildings, Roads, Water, electro mechanical, treatment plants, and other infrastructure works.

‎ይርጋለም ኮንስትራክሽን በሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በይርጋዓለም የተ/የግብ/ኢን/ ፓርክ ተጨማሪ ሦስት አዳዲስ ፕሮጀክቶች ትግበራ ላይ የውል ስምምነት ተፈራረመ። ‎የኢንጂነር...
17/06/2026

‎ይርጋለም ኮንስትራክሽን በሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በይርጋዓለም የተ/የግብ/ኢን/ ፓርክ ተጨማሪ ሦስት አዳዲስ ፕሮጀክቶች ትግበራ ላይ የውል ስምምነት ተፈራረመ።

የኢንጂነር ዘላለም ወልደአማኑኤል ዱባለ ድርጅቶች ውስጥ የሆኑት የሦስት ፕሮጀክቶች ትግበራ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡

‎ቀደም ሲል በ”Golden organic Avocado oil’’ ምርት ላይ ተሰማርተው ያሉት ኢንጂነር ዘላለም ወልደአማኑኤል በዛሬው ዕለት ስምምነቱን የፈረሙት በፓርኩ ተጨማሪ ሶስት ፕሮጀክቶች ማለትም በዘርፈብዙ የጥራጥሬ ዘይት፣ የድፍድፍ ዘይት ማጣሪያ እና የተቀናጀ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡

‎ፕሮጀክቶቹ በ12.8 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ወይንም 2 ቢሊዮን ብር የሚፈጁ ፕሮጀክቶች ሲሆኑ፤ በሙሉ አቅም ወደ ሲራ ሲገባ ለ500 ያህል ወጣቶች ቋሚ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ይሆናል፡፡

‎የውል ስምምነቱን የፈረሙት ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ኃይሉ የተራ እንደገለጹት በፓርኩ የሀገር ውስጥ ባለሀብት በዚህ ያህል ካፒታል ፕሮጀክት ሲፈረም የመጀመሪያ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ረገድ እጅግ ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡

‎የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆኑት ኢንጂነር ዘላለም ወልደአማኑኤል በበኩላቸው ፕሮጀክቶቹ ቀደም ሲል በነበረው የአቮካዶ ዘይት ፕሮጀክት ተበረታተው የጀመሯቸው መሆኑን ገልፀው፤ የሶስቱንም ፕሮጀክቶች ሼድ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቀው ወደ ምርት ሂደት እንደሚገቡ አረጋግጠዋል፡፡

የድርጅታችን ሰራተኞችና ማናኔጅምነት አካላት እንኳን ደስ አለን፣ አላችሁ!

የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!

በጋራ ኢትዮጵያን እንገነባለን!

ይርጋለም ኮንስትራክሽን

ጎልደን አቮካዶ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ግብአት መጠኑን አሳደገ። የይርጋለም ኮንስትራክሽን እህት ኩባንያ የሆነው ጎልደን አቮካዶ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ከማህበራት ከሚረከበው አቮካዶ በተጨማሪ በ...
10/06/2026

ጎልደን አቮካዶ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ግብአት መጠኑን አሳደገ።

የይርጋለም ኮንስትራክሽን እህት ኩባንያ የሆነው ጎልደን አቮካዶ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ከማህበራት ከሚረከበው አቮካዶ በተጨማሪ በሎካ አባያ የራሱ እርሻ/Farm/ ትልቅ ምርት ሰብስቧል።

ፋብሪካው በይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኝ ሲሆን በውስጡ በርካታ ፋብሪካዎችን ይዟል።

በአመት እስከ 80,000 ገበሬዎችን ካቀፉ ህ/ስራ ማህበራት የሚረከብ ይህም በተጨማሪ ለውጭ ሀገር የሚላከውን ምርት ከፍ ያደርገዋል።

ፋብሪካው በእርሻና እንዱስትሪ ላይ በመሰማራት ለሀገራችን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እያመጣ መሆኑ ይታወቃል።

ይርጋለም ኮንስትራክሽን
ጎልደን አቮካዶ ፋብሪካ

🌹ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛዉ ዓመተ ሂጅራ የታላቁ ኢድአል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ይሁንላችሁ ✨🌙Eid Mub...
27/05/2026

🌹ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛዉ ዓመተ ሂጅራ የታላቁ ኢድአል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ይሁንላችሁ ✨🌙

Eid Mubarak ✨ 🌙
Yirgalem Construction

24/05/2026

የጅግጅጋ ተለዋጭ መንገድ ግንባታን አስመልክቶ
እንኳን ደስ አላችሁ!
©ኢቢሲ

Yirgalem Construction

22/05/2026
ይርጋለም ኮንስትራክሽን ሲያከናውን የነበረው የጅግጅጋ ከተማ ተለዋጭ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጠናቅቆ ለስራ ክፍት ሆነ።  በሶማሌ ክልል የጅግጅጋ ከተማ ተለዋጭ አስፋልት ኮንክሪት ...
22/05/2026

ይርጋለም ኮንስትራክሽን ሲያከናውን የነበረው የጅግጅጋ ከተማ ተለዋጭ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጠናቅቆ ለስራ ክፍት ሆነ።

በሶማሌ ክልል የጅግጅጋ ከተማ ተለዋጭ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት መጠናቀቁን ተከትሎ ደረጃውን የጠበቀ የትራፊክ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የመንገድ ፕሮጀክቱን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ መሐመድ እና የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በጋራ መርቀውታል።

አጠቃላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ 6 ነጥብ 93 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን፣ 30 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ተገንብቷል።
መነሻውን ጅግጅጋ ከተማ መግቢያ አድርጎ ቶጎ-ጫሌ አደባባይ ላይ ያበቃው ይህ ፕሮጀክት ስራዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀዋል።

በእለቱ የኮንስርትክሽን ሚኒስቴርን ጨምሮ የክልሉ ፕሬዚዳንት በቦታው ተገኝተው መርቀው ከፍተዋል።

ለዚህ መሳካት አብራችሁን የነበራችሁ በሙሉ እናመሰግናለን!

ይርጋለም ኮንስትራክሽን!

መላው የአርሴናል ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ። ይርጋለም ኮንስትራክሽን!ገፁን ፎሎው ያድርጉ!
20/05/2026

መላው የአርሴናል ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ።
ይርጋለም ኮንስትራክሽን!
ገፁን ፎሎው ያድርጉ!

አዲስ የYirgalem Group የAI ረዳት በይፋ ስራ ጀመረ!የYirgalem Construction Group ደንበኞች በሙሉ፤ የድርጅታችንን አገልግሎቶች ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ አዲስ የAI ...
30/04/2026

አዲስ የYirgalem Group የAI ረዳት በይፋ ስራ ጀመረ!

የYirgalem Construction Group ደንበኞች በሙሉ፤ የድርጅታችንን አገልግሎቶች ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ አዲስ የAI ረዳት (Chatbot) ማቅረባችንን በደስታ እንገልጻለን። ይህ AI ረዳት በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀናት የሚሰራ ሲሆን፥ ስለ አምስቱም እህት ኩባንያዎቻችን መረጃ ይሰጥዎታል።

ምን መጠየቅ ይችላሉ?

🏗 ይርጋለም ኮንስትራክሽን: ስለ መንገድና ህንፃ ግንባታዎች እንዲሁም ኮሪደር ስራን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮጀክቶች

💧 ቤዛ የተፈጥሮ ምንጭ ውሃ: የውሃ አቅርቦትና ስርጭትን ለማወቅ

🥑 ጎልደን የአቮካዶ ዘይት: ወደ ውጭ ስለሚላኩ ኦርጋኒክ ምርቶች

🍯 ፋሚሊ ማር: ስለ ማር ዝግጅትና ሽያጭ

☕️ ዘላለም ቡና: ስለ ሲዳማ ቡና ላኪነታችን መረጃ ለማግኘት

እንዴት ያገኙናል?
🌐 ድረ-ገጻችን: yirgalemconstruction.com ላይ በመግባት ከታች ቀኝ የቻት ምልክቷን ይጫኑ።
📲 በቴሌግራም: በዚህ ሊንክ ያገኙናል:

የወደፊቱን የYirgalem Group ቴክኖሎጂ ዛሬውኑ ይጠቀሙ!

የረዳን እግዚአብሄርን እናመሰግናለን!
https://t.me/YirgalemGroup_bot

እንኳን ደስ አለን፣ አላችሁ!ዛሬ በዲላ ከተማ የ5.05 ኪ.ሜ የአስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት የደ/ኢ/ክ/መንግስት ር/መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በይፋ ስራ አስጀምረናል!!ፕሮግራሙ ...
25/04/2026

እንኳን ደስ አለን፣ አላችሁ!

ዛሬ በዲላ ከተማ የ5.05 ኪ.ሜ የአስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት የደ/ኢ/ክ/መንግስት ር/መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በይፋ ስራ አስጀምረናል!!

ፕሮግራሙ በሀገር ሽማግሌዎች፣ በሀይማኖት አባቶች ተመርቆ የተከፈተ ሲሆን ፕሮጀክቱ የዲላ ከተማን ይበልጥ የሚያሳምርና ምቹ የሚያደርጋት እንደሚሆን ይጠበቃል።

የረዳንን እግዚአብሄርን እናመሰግናለን!

For all new and updates follow us on
Website: https://yirgalemconstruction.com
Facebook: https://facebook.com/yirgacons
Tiktok: https://www.tiktok.com/
Instagram: https://instagram.com/yirgacon
Telegram: https://t.me/yirgacon
Twitter: https://x.com/yirgacon
Youtube: https://www.youtube.com/
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/yirgacon
Tiktok: https://www.tiktok.com/

በጋራ ኢትዮጵያን እንገነባለን!

ይርጋለም ኮንስትራክሽን!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yirgalem Construction posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yirgalem Construction:

Share