Ovid Holding

Ovid Holding Ovid Holding is dedicated to innovation and excellence in construction, real estate, technology, and venture capital.

We deliver high-quality projects that improve communities and drive economic growth.

ካቮድ 2 ዘመናዊ መኪኖችን እና የቤት ዕቃዎችን ለዕድለኛ ደንበኞቹ ሸለመ🚗 የዲያስፖራው ደንበኛ የአንዷ መኪና ባለዕድል ሆነዋልካቮድ ኮሜርሻል ሪል ስቴት ዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ባ...
05/09/2026

ካቮድ 2 ዘመናዊ መኪኖችን እና የቤት ዕቃዎችን ለዕድለኛ ደንበኞቹ ሸለመ

🚗 የዲያስፖራው ደንበኛ የአንዷ መኪና ባለዕድል ሆነዋል

ካቮድ ኮሜርሻል ሪል ስቴት ዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ባከናወነው “የካቮድ ልዩ
ሎተሪ” እጣ አወጣጥ ስነ-ስርአት፤ 2 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችንና
የቤት ዕቃዎችን ለደንበኞቹ ሸልሟል።

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ባለሙያዎች በተገኙበት የእጣ አወጣጥ መኪና ከተሸለሙት አንዱ በካናዳ የሚኖሩ ደንበኛ ሲሆኑ፤ እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኦቪድ ፈርኒቸር የቤት ዕቃዎችም ለእድለኞች ተሸልመዋል።

ኩባንያው በመርሃ ግብሩ የደንበኞች
አድናቆት እና “አራዳው ነጋዴ” የተሰኘውን
ብራንድ በይፋ ያስተዋወቀ ሲሆን፤ ከ300 በላይ ደንበኞችና እንግዶች ታድመዋል።

የካቮድ ኮሜርሻል ሪል እስቴት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የምወድህ ታደለ ባስተላለፉት መልዕክት የካቮድ የንግድ ስኬት ከደንበኞቹ
እምነትና ድጋፍ እንደሚጀምር በማስታወስ፤
“ካቮድ የንግድ ቦታ አቅራቢ የሪል እስቴት
ኩባንያ ብቻ ሳይሆን፣ ደንበኞቹ ሃብትና
የንግድ ስኬት እንዲገነቡ
የሚያግዝ አጋር ነው።” ብለዋል።

ካቮድ በቀጣይ የኢትዮጵያን የንግድ ማዕከላት ገበያ በፈጠራ፣ በጥራት፣ በግልጽነትና በደንበኛ ተኮር አገልግሎት ለመምራት ቁርጠኛ መሆኑንምገልጸዋል።

የኦቪድ ሆልዲንግስ ቺፍ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ኦፊሰር አቶ መኮንን ተሾመ
በበኩላቸው፤ የኩባንያዎቹ የንግድ ፍልስፍና
በደንበኛ እምነት፣ በጥራትና በረጅም ጊዜ አጋርነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን በመግለጽ፣ “ዛሬ የተገናኘነው እጣ ለማውጣት ብቻ
ሳይሆን፣ ከደንበኞቻችን ጋር የገነባነውን እምነት ለማክበር ነው። ኦቪድ ሆልዲንግስ ሁሌም ደንበኛውን በስኬቱ ማዕከል ያደርጋል። ካቮድም ይህንን እሴት በንግድ ሥራው ውስጥ በተግባር እያሳየ ነው።” ብለዋል።

24/08/2026
ኦቪድ ሆልዲንግስ እና የቻይናው ጂአንግሼ ኩባንያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙኦቪድ ሆልዲንግስ ከእህት ኩባንያዎቹ አንዱ በሆነው በኦቪድ የመንገድና ውሃ ሥራዎች ኃ.የተ.የግ.ማ. አማካኝነ...
21/08/2026

ኦቪድ ሆልዲንግስ እና የቻይናው ጂአንግሼ ኩባንያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

ኦቪድ ሆልዲንግስ ከእህት ኩባንያዎቹ አንዱ በሆነው በኦቪድ የመንገድና ውሃ ሥራዎች ኃ.የተ.የግ.ማ. አማካኝነት ከቻይናው ጂአንግሼ የውሃ እና የሃይድሮ ፖወር ግንባታ ኩባንያ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ (Jiangxi Water and Hydropower Construction Co., Ltd. (JWHC) - Ethiopian Branch) ጋር በትልልቅ የውሃ ሥራዎች ልማት ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

በኦቪድ ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ብዙዓለም ታዬ እና በጂአንግሼ (Jiangxi) ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ሺያኦ ዌይ (Mr. Xiao Wei) ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነቱ ግድቦችን፣ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን፣ ትልልቅ ቦዮችን እና የውሃ አቅርቦት መሠረተ ልማቶችን ጨምሮ ሰፋፊ የውሃ ዘርፍ ግንባታ ሥራዎችን በጋራ ለማከናወን የሚያስችል አዲስ የአጋርነት ማዕቀፍ እንደሆነ ተነግሯል።

ስምምነቱ ሁለቱን ኩባንያዎች በትልልቅ የውሃ ፕሮጀክቶች ልማት፣ የጨረታ ዉድድር እና የፕሮጀክት ግንባታ ስራዎችን በጋራ ለማከናወን እንደሚያስችላቸው በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ትብብሩ የጂአንግሼን ሰፊ ዓለም አቀፍ የኢንጂነሪንግ ልምድና ቴክኒካዊ አቅም ከኦቪድ ሆልዲንግስ ጠንካራ አቅምና ሰፊ የግንባታ ፕሮጀክት ልምድ ጋር በማጣመር በዘርፉ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በብቃት ለማልማትና ለመፈጸም ያለመ እንደሆነም ተነግሯል።

(ኦቪድ ሆልዲንግስ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን)

OVID Holdings and JWHC Sign Water Works Development Partnership AgreementOvid Holdings, through one of its subsidiaries—...
21/08/2026

OVID Holdings and JWHC Sign Water Works Development Partnership Agreement

Ovid Holdings, through one of its subsidiaries—OVID Road and Water Works PLC—has signed a strategic partnership agreement with the Ethiopian branch of China’s Jiangxi Water and Hydropower Construction Co., Ltd. (JWHC) to collaborate on the development and construction of major water works projects.

The Memorandum of Understanding (MoU) was signed on August 17, 2026, by OVID Holdings Deputy CEO Engineer Bizualem Taye and JWHC General Manager Mr. Xiao Wei.

The agreement establishes a framework for joint venture initiatives focused on high-impact water projects, including dams, irrigation schemes, canals, and water supply infrastructure.

According to the signatories, the agreement encompasses joint business development, bidding, and ex*****on for major water-related projects.

It also aims to combine JWHC’s extensive international engineering experience and technical capabilities with OVID’s strong local operational presence and diverse construction portfolio.

(Ovid Holdings Public Relations and Communication)

የኦቪድ አመራሮችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ አከናወኑየኦቪድ ሆልዲንግስ እና በስሩ የሚገኙ እህት ኩባንያዎች የሥራ አመራሮች እና ሠራተኞች "ተስፋን እንትከል" በሚል መርህ ዛሬ ነሃሴ 7 ቀን 2...
13/08/2026

የኦቪድ አመራሮችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ አከናወኑ

የኦቪድ ሆልዲንግስ እና በስሩ የሚገኙ እህት ኩባንያዎች የሥራ አመራሮች እና ሠራተኞች "ተስፋን እንትከል" በሚል መርህ ዛሬ ነሃሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አከናውነዋል።

በመርሃ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ የዋና መስሪያ ቤቱን የኮር ቲም በመወከል ንግግር ያደረጉት የኦቪድ ሆልዲንግስ የሼርድ ሰርቪስስ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ፍሬዘር ደበላ፤ ኩባንያው በአጠቃላይ የፕሮጀክት ዲዛይንና ትግበራዎች ውስጥ ለብሔራዊው የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲ እና ለአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ በማስታወስ፤ በስፋት የሚታወቅበት የአልሙኒየም ፎርምዎርክ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂም የዚህ አካል መሆኑን በአብነት ጠቅሰዋል።

ኩባንያው በፕሮጀክቶቹ ብክለትን ለመከላከልን፣ ደህንነትን ለማረጋገጥና ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ ሰፋፊ የማህበራዊ ኃላፊነት ስራዎችን እንደሚያከናውንም አመልክተዋል።

የካቮድ ኮመርሻል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ የምወድህ ታደለ በበኩላቸው፤ ኩባንያው የችግኝ ተከላንና የደን ልማትን ተቋማዊ ባህል ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸው፤ የዛሬው መርሃ ግብርም እንደ ተቋም ለአረንጓዴ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሜ ያረጋገጠበት መሆኑን ተናግረዋል።

የኦቪድ ሪል እስቴት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰናይ ሸዋፈራው በበኩላቸው፤ ኩባንያው ባለፈው አመት በገላን ጉራ ፕሮጀክት ያደረገውን ተከላ ጨምሮ ላለፉት 7 አመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በርካታ ችግኞችን መትከሉን አስታውሰው፤ የዛሬው ተከላ የተከናወነው ከቢሮው አቅራቢያ መሆኑ ለእንክብካቤ እንደሚያመችና ለዚህም ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል።

📸 Sami Camera
Behailu Azeze

(ኦቪድ ሆልዲንግስ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን)

OVID Holdings Begins Organizational Renewal Kick-off Workshop in BishoftuA comprehensive institutional transformation ki...
04/08/2026

OVID Holdings Begins Organizational Renewal Kick-off Workshop in Bishoftu

A comprehensive institutional transformation kick-off workshop of the OVID Holdings opened yesterday, August 3, 2026, at Kuriftu Resort & Spa in Bishoftu town.

Opening the workshop with his remarks, Founder and Chief Executive Officer of OVID Holdings Mr. Yonas Tadesse underlined that it is time to transform OVID.

“If we do not renew our structure now, we will stall. The window for change is right now. This transformation is not just for decoration; it is a business necessity,” he pointed out.

The workshop is led by Antra Business Group in Ethiopia compromising it's Managing Director Dr. Anteneh Tegegn as well as other prominent business strategy leaders - Prof. Pikay Richardson, Prof. Mathew Tsamenyi and Dr. Anderson Uvie Emegbo.

The workshop, which plays a pivotal role in charting the company's overall future transformation trajectory will continue through today.

📸 Sami Camera
(Ovid Holdings Public Relations and Communication)

Job Title: Chief Financial Officer (CFO)Required Number: One Department/Unit: CFO Office Report To: Deputy Chief Executi...
23/07/2026

Job Title: Chief Financial Officer (CFO)

Required Number: One
Department/Unit: CFO Office
Report To: Deputy Chief Executive Officer; OVID Holdings
Location: Addis Ababa/Gerji, Head Office

JOB SUMMARY

OVID Holdings is seeking a visionary, strategic, and resilient Corporate Chief Financial Officer to lead the financial architecture of our conglomerate. Operating across diverse subsidiaries, spanning Construction, Real Estate, Manufacturing, Academy, Furniture, Industries, and Trading, OVID Holdings requires a seasoned executive who can balance centralized corporate governance with the operational agility of independent subsidiary teams.

As the Corporate CFO, you will act as the principal financial strategist, business partner to the CEO, and steward of capital allocation. You will not manage day-to-day bookkeeping for individual companies; instead, you will architect consolidated financial oversight, optimize enterprise-wide capital structures, drive corporate-level risk management, and spearhead transformative growth initiatives.

Apply on: [email protected]

23/07/2026

ኦቪድ አካዳሚ በሀገራዊ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና (TVET) ማዕቀፍ መሰረት ሀገራዊ እውቅናና ሰርትፍኬሽን ያለው የሪል ስቴት ሽያጭ እና ግብይት ሙያዊ ስልጠና ፕሮግራም ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነው።

ይህ የስልጠና ፕሮግራም ስራ አጥ ወጣቶችንና በሌላ ሙያ (ስራ) ላይ ሆነው ወደ ሪል ስቴት ሽያጭና ግብይት ሙያ መግባት ለሚፈልጉ ደረጃውን የጠበቀና ሀገራዊ እውቅናና ሰርትፍኬሽን ያለው ስልጠና እንዲያኙ በማድረግ የስራ እድልን የመፍጠርና የማስፋት እንዲሁም የዘርፉን የሙያ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

ስለሆነም የእርስዎ ሃሳብ ለዚህ የስልጠና መርሃ ግብር ውጤታማነት ወሳኝ በመሆኑ ትክክለኛ መረጃ እንዲሰጡን በትህትና አንጠይቃለን።

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfl6PSzyl1LW-pooChKZTyzZK00iQq7vBifH-jY36uPeQUoQw/viewform?usp=publish-editor

ከኦቪድ እህት ኩባንያዎች - ኦቪድ ማኑፋክቸሪንግበኦቪድ ሆልዲንግስ ስር የሚገኘው ኦቪድ ማኑፋክቸሪንግ፣ የኩባንያውን የግብዓት አቅርቦት ሰንሰለት ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ በ2013 ዓ.ም የተ...
22/07/2026

ከኦቪድ እህት ኩባንያዎች - ኦቪድ ማኑፋክቸሪንግ

በኦቪድ ሆልዲንግስ ስር የሚገኘው ኦቪድ ማኑፋክቸሪንግ፣ የኩባንያውን የግብዓት አቅርቦት ሰንሰለት ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ በ2013 ዓ.ም የተመሰረተ ኩባንያ ነው።

ከራሱ ምርቶች ባለፈ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ስትራቴጂያዊ ትስስር በመፍጠር፣ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን ከፍተኛ የግብዓት ፍላጎት ያለማቋረጥ የማሟላት ዓላማ አንግቦ የተቋቋመው ድርጅቱ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ልዩ ልዩ የኮንክሪት ውህዶችን እና ተያያዥ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በስፋት በማምረት፣ በማቅረብና በማስተዋወቅ የግንባታውን ዘርፍ በማዘመን ላይ ይገኛል።

ኦቪድ ማኑፋክቸሪንግ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውንና ለ«ኩምካንግ አልሙኒየም ፎርም ወርክ» የሚያገለግለውን የሰልፍ ኮምፓክትድ ኮንክሪት በከፍተኛ ጥራት በማምረትና በአገር ውስጥ በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ የሚገኝ አገር በቀል ድርጅት ነው፡፡

አስተማማኝ አቅርቦትን በማሟላት የግንባታ አፈጻጸምን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው ድርጅቱ፣ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ከ240 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ የኮንክሪት ውህድ በማምረት ከ50 በላይ ለሚሆኑ የኦቪድ ሆልዲንግስ ፕሮጀክቶች አቅርቧል።

የማምረት አቅሙን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገ የሚገኘው ኦቪድ ማኑፋክቸሪንግ በአዲስ አበባ (ጎሮ፣ ጫካ እና ገላን ጉራ) እና በጅማ ከተማ በሚገኙ 4 ዘመናዊ የኮንክሪት ማምረቻ ጣቢያዎቹ በሰዓት 300 ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ምርት የማምረት አቅም ገንብቷል፡፡

ከተቋሙ ዋና ዋና ምርቶች መካከል ጥራት ያለው የኮንክሪት ውህድ፣ ሰልፍ ኮምፓክትድ ኮንክሪት፣ የተለያዩ የጠጠር ምርቶች፣ የተዘጋጀ አሸዋ፣ የወለል ንጣፎች እና ብሎኬቶች ይጠቀሳሉ፡፡

📸 ሳሚ ካሜራ
በሃይሉ አዘዘ
(ኦቪድ ሆልዲንግስ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን)

Job Title: Chief Technology Officer (CTO)Required Number: One Department/Unit: ICT  Report To: Chief Corporate Shared Se...
22/07/2026

Job Title: Chief Technology Officer (CTO)

Required Number: One
Department/Unit: ICT

Report To: Chief Corporate Shared Services Officer; OVID Holdings
Location: Addis Ababa/Gerji, Head Office

JOB SUMMARY

The Chief Technology Officer (CTO) serves as the strategic technology leader at the Holdings level for OVID Holdings, a massive conglomerate comprising more than 30 subsidiaries. Operating across diverse sectors with a strong emphasis on construction and real estate, the CTO is responsible for shaping and executing the overarching ICT vision, digital transformation roadmap, and technology infrastructure. This role provides corporate-level governance, standardization, and oversight of all ICT-related activities across the entire subsidiary network, ensuring scalable, secure, and innovative technology solutions that drive enterprise-wide efficiency and competitive advantage.

Apply on: [email protected]

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ovid Holding posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ovid Holding:

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed Contractor?

Share