20/08/2019
324 ሚሊዮን አተረፈ
======
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2011 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ብር 325 ሚሊዮን ለማትረፍ አቅዶ ብር 324 ሚሊዮን ወይም ከዕቅዱ 100.5 በመቶ አተረፈ፡፡ ይህ ትርፍ ከ2010 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ15 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
ኮርፖሬሽኑ ይህንን ትርፍ ሊያገኝ የቻለው በዕቅድ ዘመኑ በውሃና ኢነርጂ፣በህንጻና ከተማ ልማት፣በትራንስፖርት፣በጂኦቴክኒካል ምህንድስና፣ በቅየሳና ጂኦስፓሻል፣በምርምር፣ላብራቶሪ እና ስልጠና ዘርፎች ሊያከናውን ከያዛቸው የዲዛይን፣የቁጥጥርና የማማከር ተግባራት ብር 1.09 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት አቅዶ ብር 769.1 ሚሊዮን ወይም የዕቅዱን 70 በመቶ ገቢ በማግኘቱ እንደሆነ የኮርፖሬሽኑ ዕቅድ አፈጻጸም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ነሐሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በተገመገመበት ወቅት ተገልጿል፡፡