Dera Wereda REDD+ Investment Program

Dera Wereda REDD+ Investment Program ደን በማልማት የአየር ንብረት ለውጥን በጋራ እንከላከል!!!

ስራዎቻችን በከፊል....
04/06/2023

ስራዎቻችን በከፊል....

በወፍ አርግፍ ቀበሌ የአጃፈጅ ደን ልማት አሁናዊ ሁኔታ
10/10/2022

በወፍ አርግፍ ቀበሌ የአጃፈጅ ደን ልማት አሁናዊ ሁኔታ

በወፍ አርግፍ ቀበሌ በደን ልማት ስራዎች ላይ የገበሬ በዓልና የልምድ ልዉዉጥ ፕሮግራም ተካሄደየደራ ወረዳ ሬድ ፕላስ ፕሮግራም የደን ልማት ስራዉን ከሚያካሂድባቸዉ ቀበሌዎች ዉስጥ  አንዱ በሆ...
26/06/2021

በወፍ አርግፍ ቀበሌ በደን ልማት ስራዎች ላይ የገበሬ በዓልና የልምድ ልዉዉጥ ፕሮግራም ተካሄደ
የደራ ወረዳ ሬድ ፕላስ ፕሮግራም የደን ልማት ስራዉን ከሚያካሂድባቸዉ ቀበሌዎች ዉስጥ አንዱ በሆነዉ በወፍ አርግፍ ቀበሌ በፕሮጀክቱ ደል ልማት ስራዎች ላይ የልምድ ልዉዉጥና የገበሬ በዓል ተካሂዷል፡፡
ፕሮጀክቱ በወረዳዉ ዉስጥ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ ስዉን ሲሰራ የቆየ ቢሆንም ወፍ አርግፍ ቀበሌ 2011 ዓ/ም በፕሮጀክቱ በመታቀፍና በቀበሌዉ ዉስጥም ችግኝ ጣቢያ በማቋቋም የደን ልማት ስዉን በሰፊዉ የጀመረ ቢሆንም ባለፉት ሁለት አመታት በቀበሌዉ ዉሥጥ ያሉ የተፈጥሮ ደኖችን ከንክኪ ከልሎ እንዲያገግሙ በማድረግ (ANR) ብዙ ስራዎችን የሰራ ቢሆንም በአዲስ ደን ልማት ዘርፍ (AR) ስራዎች ላይ በቀበሌዉ ዉስጥ ያለዉን አጃፈጅ የተከላ ቦታ ከተጠቃሚ አርሶ አደሮች ጋር የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ በመድረስ በሁለት አመት ዉስጥ ከ17 ሄክታር በላይ የሚሆነዉን ቦታ በደን መሸፈን ተችሏል፡፡ በያዝነዉም ዓመትም የቀረዉን ቦታ ሙሉ በሙሉ በችግኝ ለማልበስ “የተራቆተ መሬት ለትዉልድ አናወርስም” የሚል መሪ ቃል በመያዝ የዘመቻ ስራዉን አጠናክረዉ ቀጥለዋል፡፡
በቀበሌዉ ግብርና ጽ/ቤት አዘጋጅነት በቀን 16/10/2013 ዓ/ም በቀበሌዉ ዉስጥ ካሉት ሌላኛዉ የፕሮጀክቱ የተከላ ቦታ የሆነዉ የሀሙስ ገበያ የተከላ ቦታ ተጠቃሚዎች ከነባሩ የደን ልማት ቦታዉ አጃፈጅ የተከላ ቦታ ተጠቃሚዎች በጋራ በመሆን የልምድ ልዉዉጥ እና የመስክ የስራ ጉብኝት ፕሮግራም ተካሒዷል፡፡

03/06/2021

ኢትዮጽያን እናልብስ!!

03/06/2021

Reducing Emission from Deforestation and forest Degradation.

የደራ ወረዳ ሬድ ፕላስ ኢንቨስትመንት ፕሮግራም ለ2013 ዓ.ም የደን ችግኝ ተከላ የሚውሉ ከ2.5 ሚሊየን በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን ማዘጋጀቱን ገለፀ፡፡የደራ ወረዳ ...
02/06/2021

የደራ ወረዳ ሬድ ፕላስ ኢንቨስትመንት ፕሮግራም ለ2013 ዓ.ም የደን ችግኝ ተከላ የሚውሉ ከ2.5 ሚሊየን በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን ማዘጋጀቱን ገለፀ፡፡
የደራ ወረዳ ሬድ ፕላሽ ኢንቨስትመንት ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ አላዘር ጫንያለው እንደተናገሩት ሬድ ፕላስ ኢንቨስትመንት ፕሮግራም በዋናነት ትኩረት ሰጦ ከሚሰራቸው ስራዎች የሀገሪቱን የደን ሽፋን ከፍ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡ በዚህም መሰረት እንደ ደራ ወረዳ ለ2013 የደን ችግኝ ተከላ የሚውሉ በወረዳ በሚገኙ 7 የችግኝ ጣቢያዎች አማካኝነት 2 ሚሊየን 578 ሺ 800 ችግኞችን ማፍላት ተችሏል፡፡ ማፍላት ከተቻለው ችግኝም 242 ሺ የሀገር ውስጥ ዝርያ ያላቸው ሲሆኑ 2ሚሊየን 336 ሺ 800 ደግሞ የውጭ ሀገር ዝርያ ያላቸው ችግኞች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ማህበረሰቡን በማወያየትና ግንዛቤ በመፍጠር ከግጦሽ ወደ ተከላ ቦታነት በማስገባት የስምምነት ቃለ ጉባኤ በመያዝ በወረዳው ውስጥ 580 ሄክታር የመትከያ ቦታ ማዘጋጀት ተችሏል ብለዋል፡፡
ሌላው በ2013 ዓ.ም የተዘጋጀው የችግኝ ብዛት በ2012 ዓ.ም ተመሳሳይ ወቅት ከተዘጋጀው ችግኝ ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ ጭማሪ አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ሌላው በ2012 ዓ.ም በወረዳው የተለያዩ ቦታዎች በሬድ ፕላስ ኢንቨስትመንት ፕሮግራም አማካኝነት የተተከሉ ችግኞችን የመጽደቅ ምጣኒያቸው 89 በመቶ በመሆኑ የተሻለ ነበረ ብለዋል፡፡
አስተባባሪው አክለውም ይህ ፕሮጀክት በውጤታማነቱ ቀጥሎ የወረዳውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግና የወረዳውን የደን ሽፋን ከፍ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካል የኔባይነት ስሜት ተሰምቶት በመስራት የየድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ ሌላው የተዘጋጀው ችግኝና ለተከላ ልየታ ከተደረገው የቦታ ስፋት አንፃር የተዘጋጀው ችግኝ መጠኑ ዝቅ ያለ በመሆኑ ከመንግስትና በተዘጋጀና በግለሰቦች በተዘጋጁ ችግኞች ለመግዛት እቅድ አውጥተን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡
17/09/13
እስቲበል አለኸኝ

Address

Anbesame

Telephone

+251920772121

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dera Wereda REDD+ Investment Program posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share