MTGC

MTGC Melaku Tesfaye General Contractor

26/08/2026
የታማኝ ግብር ከፋይነት ሽልማት 2018!  ! እናመሰግናለን!  ይቀጥላል!
26/08/2026

የታማኝ ግብር ከፋይነት ሽልማት 2018! !
እናመሰግናለን!
ይቀጥላል!

የዶ/ር ራድኤል B+G+10 የሪል ስቴት ፕሮጀክት ግንባታ ስራ በይፋ ተጀመረ።ከመላኩ ተስፋዬ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ጋር ስምምነት የተፈረመለት B+G+10 የሪል ስቴት ፕሮጀክት ግንባታ ስራ በይፋ...
26/04/2026

የዶ/ር ራድኤል B+G+10 የሪል ስቴት ፕሮጀክት ግንባታ ስራ በይፋ ተጀመረ።

ከመላኩ ተስፋዬ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ጋር ስምምነት የተፈረመለት B+G+10 የሪል ስቴት ፕሮጀክት ግንባታ ስራ በይፋ ተጀመረ። በከተማ እምብርት ላይ የሚገነባውና ባለ 12 ወለል (B+G+10) የሆነው ዘመናዊ የሪል ስቴት ፕሮጀክት፣ ሁሉንም አስፈላጊ የቅድመ-ግንባታ ዝግጅቶች በማጠናቀቅ በይፋ የግንባታ ሥራው ተጀምሯል።

ይህ ፕሮጀክት ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ እና የመስሪያ አካባቢ ለመፍጠር ያለንን ራዕይ የሚያንጸባርቅ ነው። የግንባታ ሥራውን ለማከናወን ውል የገባው መላኩ ተስፋዬ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ለግንባታ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ የግንባታ ስራውን ጀምሯል። የግንባታው ጅማሬ በታቀደለት መርሃ-ግብር መሠረት መከናወኑ፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን ጠንካራ ሙያዊ ትብብር የሚያሳይ ሲሆን፤ ስራውን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ የሚስችል መሆኑን ማሳያ ነው።

በመጨረሻም፣ ይህ ፕሮጀክት ከግንባታ ባለፈ ለከተማችን ውበትና ለቤቶች ልማት ዘርፍ የራሱን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ፍላጎታችን መሆኑን እየገለጽን፤ የሥራ ሂደቱን በየደረጃው የምናሳውቅ መሆኑን እናረጋግጣለን።

የዶ/ር ራድኤል ገምታ B+G+10 የሪል ስቴት ህንጻ ፕሮጀክት ግንባታ የውል ስምምነት ተፈጸመ።ድሬዳዋ | ዶ/ር ራድኤል ገምታ ሪል ስቴት በድሬዳዋ ከተማ እምብርት ላይ ለሚገነባው ዘመናዊ ባለ ...
23/04/2026

የዶ/ር ራድኤል ገምታ B+G+10 የሪል ስቴት ህንጻ ፕሮጀክት ግንባታ የውል ስምምነት ተፈጸመ።

ድሬዳዋ | ዶ/ር ራድኤል ገምታ ሪል ስቴት በድሬዳዋ ከተማ እምብርት ላይ ለሚገነባው ዘመናዊ ባለ 12 ወለል (B+G+10) የሪል ስቴት ፕሮጀክት ግንባታ ለማከናወን በከተማዋ በግንባታ ዘርፍ ከታወቀው ከመላኩ ተስፋዬ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ጋር በይፋ ስምምነት ተፈራርሟል። ይህ የሪል ስቴት ፕሮጀክት ጥራቱን የጠበቀ የመኖሪያ እና የመስሪያ መንደር ለመገንባት የታለመ ሲሆን፣ በዲዛይንና በግንባታ ጥበብ ረገድ አዲስ ምዕራፍ ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ዶ/ር ራድኤል ሪል ስቴትን በመወከል የተገኙት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እንጉዳይ አማረ እንደተናገሩት፤ ይህ የሚገነባው ህንጻ ለከተማዋ ምቹ እና ዘመናዊ የመኖሪያ እና የመስሪያ መንደር እንደሚሆን ያላቸው እምነት ገልጸዋል። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሳይጀምር ቢቆይም ከረዥም ጊዜ እልህ አስጨራሽ ትጋት እና ትዕግስት በኋላ እውን በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረው፤ ከተቋራጩ ጋር ከዚህ በፊት በነበራቸው መልካም የሥራ ግንኙነት እና በከተማው ውስጥ በተገነቡ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ላይ ባሳየው መልካም አፈጻጸም የተነሳ፤ ይህን ፕሮጀክት ለመስጠት ሙሉ እምነት አሳድረዋል። ሥራው በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት ከግብ እንደሚደርስ ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል።

የሥራ ተቋራጩን በመወከል ፊርማቸውን ያኖሩት የድርጅቱ ዋና የሥራ መሪ(Chief Operation Officer) ኢር መልካምሥራ አዳነ በበኩላቸው የተጣለባችውን እምነት በመረዳት የግንባታ ሥራውን በተቀመጠለት የጊዜ ገደብና በላቀ ጥራት ለማጠናቀቅ ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል::

"የአረጋውያን ድጋፍ እንሩጥ!" 2018@ Dire Dawa
04/01/2026

"የአረጋውያን ድጋፍ እንሩጥ!" 2018@ Dire Dawa




Address

Dire Dawa
663

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MTGC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to MTGC:

Shortcuts

Share