የኢትዮጵያ ደን ልማት ሀዋሳ ማዕከል

የኢትዮጵያ ደን ልማት ሀዋሳ ማዕከል Ethiopian Forest Development
Hawassa Center Ethiopian Environment and Forest Research Institute (EEFRI), Hawassa Environment and Forest Research Center (HEFRC)
(3)

እንጉዳይ 🍄
15/11/2025

እንጉዳይ 🍄

11/11/2025

Ethiopia tapped to host COP32 climate summit

Click the link in the comments below.

11/11/2025

ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ ተመረጠች።

አዲስ አበባ፣
ሕዳር 2፣ 2018 ዓ.ም
*************®**********
ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ32) ለማስተናገድ ተመረጠች፡፡

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም በርካታ ተግባራትን እያከናወነች ሲሆን፥ 32ኛውን ጉባኤ ለማስተናገድ ባለፈው መስከረም ወር ጥያቄ አቅርባለች፡፡

በብራዚል ቤለም እየተካሄደ በሚገኘው 30ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ30) ተሳታፊ ሀገራት የኢትዮጵያን ጥያቄ በመርህ ደረጃ መቀበላቸው ተገልጿል፡፡

የኮፕ30 ጉባኤ ፕሬዚዳንት አንድሬ ኮሪያ ዶ ላጎ የጉባኤው ተሳታፊ ሀገራት ሁነቱን እንድታስተናግድ መስማማታቸውን ገልጸው፥ በዛሬው ዕለት በይፋ ኃላፊነቱን ትቀበላለች ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል በቀጣዩ ዓመት የሚካሄደውን 31ኛውን ጉባኤ ለማስተናገድ ቱርክ እና አውስትራሊያ ጥያቄ ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን፥ እስካሁን ውሳኔ ላይ አልተደረሰም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ሀገራችን ከቅርብ አመታት ወዲህ እያስመዘገበች ባለው ዘርፈ ብዙ ስኬት የተነሳ በርካታ ዓለማቀፍ፣ አህጉር አቀፍና ቀጠናዊ ሁነቶችን ለማዘጋጀት ተመራጭ እየሆነች መምጣቷ ይታወቃል።

11/11/2025

ለኢትዮጵያ የደን ልማት የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት አግዛለሁ - ፋኦ
አዲስ አበባ፣
ሕዳር 2 ፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)
***************®************
የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ኢትዮጵያ በደን ልማት ለምታከናውናቸው ተግባራት የፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት አግዛለሁ አለ፡፡

የፋኦ የኢትዮጵያ ተወካይ ፋራይ ዚሙድዚ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ ደኖችን መልሶ በማልማትና በመንከባከብ ረገድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባከናወነቻቸው ሰፋፊ ስራዎች መሻሻሎች ታይተዋል፡፡

በዚህም ዓለም አቀፍ የካርቦን ፋይናንስ ድጋፍ ለማግኘት ወሳኝ ሂደት ማለፏን ጠቁመው፥ ፋኦ ይህንን ጥረት እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል፡፡

የካርቦን የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ወሳኝ በሆኑት የደን ጥበቃና የመሬት መራቆትን በመቀነስ ረገድ ኢትዮጵያ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች ለማረጋገጥ ተቋማቸው ከኢትዮጵያ የደን ልማት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ድጋፉ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ይበልጥ ተጎጂ የሆኑ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልጸው፥ በዚህ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት ከፋይናንስ ድጋፍ ባሻገር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባሻገር የረዥም ጊዜ የኢኮኖሚና አካበቢያዊና ጠቀሜታን በሚያረጋግጥ መልኩ ዘላቂ የደን ልማት አስተዳደርን እየተገበረች መሆኗን አንስተዋል፡፡

ፋኦ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን የመቋቋም አቅምን በመገንባት፣ የተራቆቱ የመሬት ገጽታዎችን ወደነበሩበት በመመለስና ዘላቂ የደን አስተዳደርን በማረጋገጥ ረገድ የኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

03/11/2025
30/10/2025
23/10/2025

የመንግስት ሠራተኞች ተሻሽሎ የወጣው አዋጅ 1353/2017 ስለ ዲሲፒሊን ቅጣት ምን ይላል? For your understanding.
ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች: ክፍል አስራ ሦስት አንቀፅ 98 #አዋጁ እንዲህ ይላል። www.csc.gov.et
+++++++++++++++++++++++++
1.ሕጋዊ_ትእዛዝን ባለማክበር፣ በቸልተኝነት፣ በማልገም፣ ወይም ሆነ ብሎ የአሠራር ሥነ-ሥርዓት ወይም የመንግስትን ፖሊሲ ባለመከተል በሥራ ላይ በደል ማድረስ፤‎‎

2. ጉዳዮችን ሆን ብሎ ማዘግየት ወይም ባለጉዳዮችን ማጉላላት፤

3.ተቋምን አደጋ ላይ በሚጥል ተግባር መሠማራት ወይም ሥራ እንዳይሰራ ሆን ብሎ ማወክ ወይም ከሚያውኩት ጋር መተባበር

‎‎4. በቀላል የዲስፕሊን ቅጣት እርምጃዎች ባለመታረም ያለበቂ ምክንያት ሦስት ቀንና ከዛ በላይ ሥራ ከቀረ ወይም የሥራ ሰዓት አለማክበር፤

‎‎5. በሥራ ቦታ በጠብ አጫሪነትን መደባደብ፤

‎‎6. በልማዳዊ ስካር ወይም በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ በመመረዝ ሥራን መበደል፤

‎‎7. ጉቦ መቀበል ወይም እንዲሰጠው መጠየቅ፤

‎‎8. በሥራ ቦታ ለሕዝብ ሞራል ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈጸም፤

‎‎9. የሌብነት ወይም የእምነት ማጉደል ድርጊት መፈጸም፤‎‎

10.የማታለል ወይም የማጭበርበር ድርጊት መፈጸም፤‎‎

11. በመሥሪያ ቤቱ ንብረት ላይ ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ጉዳት ማድረስ፤

‎‎12. በሥልጣን አለአግባብ መጠቀም፤‎‎

13. በሥራ ቦታ ላይ ፆታዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት መፈፀም እና

14.በዚህ አንቀፅ ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ክብደት ያለው ሌላ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈፀም ።
_______________________________

ሠራተኛን ከሥራ አግዶ ስለማቆየት #አዋጁ ምን ይላል:
አንቀፅ 101 እና 2
++++++++++++++++++++++++++
1.ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ ከሥራ አግዶ ማቆየት የሚቻለው

(ሀ).ከተጠረጠረበት ጉዳይ ጋር አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች በማበላሸት:በመደበቅ ወይም በማጥፋት ምርመራውን ያሰናክላል : ተብሎ ከታሰበ

(ለ).በመንግስት ንብረት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያደርሳል:ተብሎ ከታሰበ

(ሐ).ከተከሰሰበት ጥፋት ክብደት አንፃር የሌሎችን ሰራተኞች ሞራል የሚነካ ወይም የተገልጋዩን ሕዝብ በመሥሪያ ቤቱ ላይ ሊኖረው የሚገባውን እምነት ያዛባል:ተብሎ ከታሰበ

(መ).ተፈፀመ የሚባለው ጥፋት ከሥራ ያስወጣል ተብሎ ሲገመት

(ሠ).በአገልግሎት አሰጣጥ ተገልጋዩን ማጉላላቱ እና ማማረሩ ከበቂ መረጃና ማስረጃ ጋር ተያይዞ ለመንግስት መሥሪያ ቤቱ ሲቀርብ እና የመሥሪያ ቤቱን ገፅታ ያበላሻል :ተብሎ ሲገመት ነው።

2.በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1) መሰረት አንድ ሠራተኛ ከሥራና ከደሞዝ ታግዶ ሊቆይ የሚችለው ከሁለት ወር ለማይበልጥ ጊዜ ይሆናል።

Great job Dr. Tatek Dejene and his team
21/10/2025

Great job Dr. Tatek Dejene and his team

Address

Awassa
Hawassa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያ ደን ልማት ሀዋሳ ማዕከል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share