07/07/2026
የማይናወጠው የፖለቲካ ምሰሶ፥የአቶ አለሙ ሰውነት የረቀቀ የአመራር ጥበብና የተግባር ከፍታ!!!
*********************************************
እውነተኛ የፖለቲካ መሪነት የሚለካው በሰላም ጊዜ በሚደረግ የቃላት ሸራተታ ሳይሆን የፖለቲካ ማዕበል ሲነሳ በሚታይ የማይናወጥ ፅናት፣ አርቆ አሳቢነትና ስትራቴጂካዊ እርጋታ ነው። የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለሙ ሰውነት ዘመኑ የጠየቀውን የፖለቲካ ቁመና ተላብሰው የተገኙ የዞኑ የፖለቲካ የጀርባ አጥንትና የብረት ምሰሶ ናቸው።
አቶ አለሙ በፖለቲካው መድረክ ተራና ስሜታዊ ሽኩቻዎችን ንቀው የተዉ፣ ፖለቲካን በከፍተኛ ስሌት፣ በብስለትና በምክንያታዊነት የሚመሩ የዘመናችን የፖለቲካ ጀግና ናቸው። የእሳቸው ፖለቲካዊ ጥንካሬ በሚከተሉት አንኳር መገለጫዎች ጎልቶ ይታያል፦
1. የረቀቀ ስትራቴጂካዊ አቅምና ብስለት አቶ አለሙ የፖለቲካን ቼዝ አሻግረው የሚያዩ በሳል መሪ ናቸው።
የህዝባቸውን ስነ-ልቦና፣ የዘመናት ታሪክ፣ ባህልና ወግ ከደማቸው ጋር ያዋሀዱ በመሆናቸው ውሳኔዎቻቸው ሁሉ መሬት የረገጡና የህዝብን የልብ ትርታ የሚያዳምጡ ናቸው። ጊዜያዊና ርካሽ የፖለቲካ ትርፍን አሳዳጅ ሳይሆኑ ለአዊ ህዝብ ዘላቂ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መሰረት የሚጥሉ ፖለቲካዊ ንድፈ-ሀሳቦችን በተግባር የሚተገብሩ የዘመኑ ፖለቲከኛ ናቸው።
2. የሴራ ፖለቲካን የሚያመክን ፅኑ አለት በፖለቲካው አለም ጫጫታና የሴራ ፖለቲካ በተበራከተበት በዚህ ዘመን አቶ አለሙ ሰውነት የሀሰት ትርክቶችንና የቅጥረኞችን ጩኸት በተግባር የሚያመክኑ "ፀረ-ሴራ" ጋሻ ናቸው። እንደ
ፅኑ አለት ማዕበል የማይገፋቸው፣ የጠላትን የፖለቲካ አጀንዳ ቀድመው በማንበብ አክሽፈው ወደራሳቸው የፖለቲካ አውድ መቀየር የሚችሉ ድንቅ የፖለቲካ ጠበብት ናቸው። እሳቸው ጋር የፖለቲካ ቁማር መሞከር ከብረት ጋር መጋጨት
ነው።
1. አሰባሳቢነትና የተቋም ግንባታ የአንድ ጠንካራ መሪ ትልቁ መገለጫው ሰው ሰርቶ ማለፉ ነው። አቶ አለሙ መዋቅሩን በአንድ ልብ የሚያሰልፉ፣ የልዩነት ግድግዳዎችን አፍርሰው የአንድነት ድልድይ የሚገነቡ አሰባሳቢ ማዕከል (Center of Gravity) ናቸው። በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ጠንካራ ዲስፕሊን፣ የአላማ ፅናትና ራዕይ ያለው አመራር
በማፍራት ረገድ የተጫወቱት ሚና ተቋማዊ አቅምን የገነባና ዞኑን በፅኑ መሰረት ላይ ያቆመ ነው።
2. ተግባር ተኮር ፖለቲካ ለአቶ አለሙ ፖለቲካ ማለት መፈክር ሳይሆን የህዝብን እንባ ማበስና የልማት ጥያቄዎችን መመለስ ነው። ፖለቲካን ከወረቀት አውርደው ወደ ተግባር በመቀየር፣ ውስብስብ የሆኑ የብሄረሰብ አስተዳደሩን
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በድፍረት የፈቱ ታጋይ ናቸው። እርሳቸው የሚያምኑት በ"ተግባር ፖለቲካ" በመሆኑ፣ የህዝብን ኑሮ በማሻሻልና ሰላምን በማረጋገጥ ረገድ ተጨባጭ ድሎችን አስመዝግበዋል።
#በአጠቃላይ አቶ አለሙ ሰውነት የአዊን ህዝብ የፖለቲካ ልዕልና ለማስጠበቅ ሌት ተቀን የሚተጉ፤ ዛቻ፣ ማስፈራራትና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ከዓላማቸው ስንዝር ያህል የማያፈገፍጓቸው ቆራጥ መሪ ናቸው። የብልፅግና ፓርቲን ራዕይ ሰንቀው ዞኑን ወደተሻለ የፖለቲካ ከፍታ እየመሩ ያሉ፥ በታሪክ ማህደር ውስጥ በደማቅ ቀለም የሚፃፍ ተግባር እየፈፀሙ ያሉ የተግባር ሰው ናቸው።
አቶ አለሙ ሰውነት - ከቃላት በላይ የሆነ የተግባር ከፍታ፣ ከሴራ የፀዳ የፖለቲካ ብስለት!